Quantcast
Channel: Ethiopian News: Trusted, In-Depth Analysis | The Habesha
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13092

በትግራይ የተለያዩ ከተሞች ንጹሀን ሰዎች ጭካኔ በተሞላበት መልኩ እየተገደሉ መሆኑ ተገለጸ።

$
0
0



በትግራይ የተለያዩ ከተሞች ንጹሀን ሰዎች ጭካኔ በተሞላበት መልኩ እየተገደሉ መሆኑ ተገለጸ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 26/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ንጹሃን ሰዎች ከመንግሥት ጋር ሰርታችኋልና ከኛ ጋር
አልተባበራችሁም በሚል ምክንያት ጭካኔ በተሞላበት መልኩ እየተገደሉ መሆኑን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋጿል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከምንጮች ደረሰኝ ባለው መረጃ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ተባብራችኋል፣ የእርዳታ እህል
አከፋፍላችኋል በሚሉና መሰል ምክንያቶች በመቐለ ከተማ ብቻ 38 ንጹሃን ሰዎች ተገድለዋል።
በግፍ ከተገደሉት ንጹሃን መካከልም በኩሓ ክፍለ ከተማ ሕሹ ኣዲሱ በአሰቃቂ መንገድ የተገደለበት መንገድ የአሸባሪው ቡድን
ጭካኔ ማሳያ ነው ብለዋል ምንጮች።
በተመሳሳይ በመኾኒ የሚኖሩ ሙስሊሞች ተገድለዋል ንብረታቸው ተዘርፏል ያሉት ምንጮች፤ ንብረታቸው ከተዘረፈባቸው
ግለሰቦች ውስጥ አቶ ዓብደልቃድር ወዳኞ እንደሚገኙበት አስታውቀዋል።
እንደ ምንጮች መረጃ ይህ ገዳይ አሸባሪ የህወሓት ቡድን ማንነት ላይ ያተኮረ ግድያ እየፈጸመ ይገኛል፤ በግጀት የሚኖሩ
ሙስሊሞች ዋና ታርጌት በመሆናቸው እስካሁን ድረስ በርካቶች በግፍ ታርደዋል።
ለውጡን ደግፋችኋል የተባሉ ሰዎች ተሰብስበው በሶስት ሲኖትራክ መኪና ተጭነው ወደ ተንቤን እንደተወሰዱና ምን
እንደተፈጸመባቸው እንዳልታወቀም የመረጃ ምንጮች አስታውቀዋል።
ሕዝቡን ከዘራፊዎች ለማዳን በሚል በበጎ ፍቃደኝነት ፀጥታ ሲያስከብሩ የነበሩ ወጣቶች በመቐለ፣ሽረ እና ዓዲግራት
መረሸናቸውም ታውቋል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የኢንቨስትመን ቢሮ ኀላፊ የነበረውን አመራር በአሰቃቂ መንገድ ገድለው አስክሬኑ ቆራርጠው ለጅብ
ሰጥተው እንደነበርና ከጅብ የተረፈው አካል ተለቅሞ ባለፈው ሳምንት በመቐለ ገብርኤል ቤተክርስትያን ቢቀበርም በድጋሜ
አስክሬኑ ከመቃብር አውጥተው ለጅብ በመስጠት አረመኔያዊ ድርጊት እንደፈጸሙም ተገልጿል።
ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን የሀገር መከላከያ ሠራዊት በወጣ ማግስት በትዊተር ገጹ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት፤ በትግራይ
ክልል ባሉ የጤና ተቋማት ላይ ዝርፊያ ተፈጽሟል፤ ህዝቡም ለሰቆቃ ተዳርጓል ማለቱ ይታወቃል።
በተመሳሳይ አምንስቲ ኢንተርናሽናል በትግራይ ያሉ ንጹሃን ዜጎች የበቀል እርምጃ ሊወሰድባቸው ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው
መግለጹም አይዘነጋም።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m






Previous article“ኢትዮጵያ ዘንድሮ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ የቻለችው ሁላችንም ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ በመሥራታችን ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ


Source link

The post በትግራይ የተለያዩ ከተሞች ንጹሀን ሰዎች ጭካኔ በተሞላበት መልኩ እየተገደሉ መሆኑ ተገለጸ። first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13092