Quantcast
Channel: Ethiopian News: Trusted, In-Depth Analysis | The Habesha
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13088

አለም አቀፍ የሶማሌ ጥናቶች ኮንፍረንስ መካሄድ ጀመረ

$
0
0
አዲስ አበባ፣ሰኔ 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 14ኛው አለም አቀፍ የሶማሌ ጥናቶች ኮንፍረንስ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት መካሄድ ጀመረ ፡፡
በኮንፍረንሱ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ምሁራን፣ ከሶማሌ ላንድ ፣ ከጅቡቲ ፣ ከሶማሊያ ፣ ከኬንያና እንዲሁም ከሌሎች አካባቢዎች የተጋበዙ እንግዶች እየተሳተፉ ነው ።
አቶ ሙስጠፌ መሃመድ መድረኩ ያልተነካውን የሶማሌ ማህበረሰብ ባህል ቋንቋ እና የተለያዩ ትውፊቶችን ለተቀረው አለም በዕውቀትና በጥበብ እንዲሁም በጥናት በዳበረ መልኩ ለማውጣት የሚያግዝ አቅም እንዳለው ጠቅሰው እውቀቱን እንደ ምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የቋንቋው ተናጋሪዎችን በህቡዕ ባሳተፈ መልኩ የበለጠ ሊሰራበት ይገባል ብለዋል ።
በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር በሽር አብዱላሂ በበኩላቸው÷ መድረኩ ለዩኒቨርሲቲው ትልቅ የልምድ አቅምና ተሞክሮ መለዋወጫ ነው ብለዋል ፡፡
ኮንፍረንሱ ለሶስት ቀን የሚቆይ ሲሆን በቆይታው በአርብቶአደሩ ዘላቂ ህይወት ላይ ያተኮሩ ፣ በኢኮኖሚ ፣በታሪክ ፣ ቋንቋ ፣ ባህልና ቀጠናዊ ሰላምና ግንኙነት ላይ ያተኮረ የጥናት ፅሁፎች ይቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከሶማሌ ክልል ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኮንፍረንሱ ከ1978ዓ.ም በ14 ተቋማት የተጀመረ ሲሆን በዋናነትም በሶማሌ ባህል ፤ ቋንቋ ፤ የአርብቶአደሩ ህይወትና ኑሮ ፤ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ መስተጋብሮችና እንደ ምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ሰላምና ግንኙነት ላይ በትኩረት የተለያዩ ጥናትና ምርምሮችን ያደርጋል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

The post አለም አቀፍ የሶማሌ ጥናቶች ኮንፍረንስ መካሄድ ጀመረ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.



Source link

The post አለም አቀፍ የሶማሌ ጥናቶች ኮንፍረንስ መካሄድ ጀመረ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13088

Trending Articles