
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በበጀት አመቱ ዳያስፖራው ለሃገራዊ ፕሮጀክቶችና ወቅታዊ ጥሪዎች ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ከዚህ ውስጥ 192 ሚሊየን ብር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፣ 29 ሚሊየን ብር ለገበታ ለሃገር ፣ 282 ሚሊየን ብር ለኮቪድ 19 መከላከያ፣ 103 ሚሊየን ብር ለበጎ አድራጎት ስራዎች እንዲሁም ለመከላከያ ሰራዊት፣ 493 ሚሊየን ብር ለሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም የተደረገ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ዳያስፖራውን በማስተባበር የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብሩና ያልተገቡ ጫናዎችን የሚያለዝቡ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ስራዎች እንደተሰሩ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ተናግረዋል፡፡
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ እንድሪስ በበኩላቸው፥ የተገኘው ስኬት እንዳለ ሆኖ በቀጣይ በዕቅድ አፈጻጸሙ ላይ የተስተዋሉ ክፍተቶችን መድፈን ከተቻለ አፈጻጸሙን ከዚህ በላይ ማሳደግ እንደሚቻል ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ከዳያስፖራው ወደ ሶስት ቢሊየን ዶላር እንዳገኘች እንዲሁም 3 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 83 ፕሮጀክቶች ወደ ስራ መግባታቸው ተገልጿል፡፡
ፕሮጀክቶቹ ለ13 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠራቸውን የኤጀንሲው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
The post ዳያስፖራው ለሃገራዊ ፕሮጀክቶችና ወቅታዊ ጥሪዎች ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.
The post ዳያስፖራው ለሃገራዊ ፕሮጀክቶችና ወቅታዊ ጥሪዎች ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.