Quantcast
Channel: The Habesha: Latest Ethiopian News, Analysis and Articles
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

“አሸባሪው ህወሃት ከስልጣን ውጪ ለትግራይ ሕዝብ ጥቅምና ህልውና ዴንታ እንደሌለው በተግባር አሳይቷል” ዶክተር አረጋዊ በርሄ

$
0
0

“አሸባሪው ህወሃት ከስልጣን ውጪ ለትግራይ ሕዝብ ጥቅምና ህልውና ዴንታ እንደሌለው በተግባር አሳይቷል” ዶክተር አረጋዊ በርሄ

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 24/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ህወሃት ከስልጣን ውጪ ለትግራይ ሕዝብ ጥቅምና ህልውና ዴንታ እንደሌለው በተግባር አሳይቷል ሲሉ የትግራይ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ትዴፓ) ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ገለጹ፡፡

ዶክተር አረጋዊ በርሄ በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ለኢዜአ መረጃ ሰጥተዋል፡፡

የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል የወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃ ካጠናቀቀበት ማግስት ጀምሮ የትግራይ ሕዝብ ለችግር እንዳይዳረግ የሰብዓዊ ድጋፍ በማድረግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ነገር ግን አሸባሪው የህወሓት ቡድን መንግሥት ለሕዝብ የሚያደርሰውን ሰብዓዊ ድጋፍ ሲዘርፍና ለሕዝብ እንዳይደርስ ሲያስተጓጉል መቆየቱንም ነው የገለጹት።

የሽብር ቡድኑ አባላት የሰብዓዊ ድጋፉን ከሕዝብ ጉሮሮ በመንጠቅ ለራሳቸው መጠቀሚያ ሲያደርጉት መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ቡድኑ የትግራይ ሕዝብ እንዳይቸገር የሰባዓዊ ድጋፍ ለማዳረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የክልሉ ተወላጆችንና ከተለያዩ አከባቢ የመጡ ባለሙያዎችን ሲያንገላታና ሲገድል መቆየቱንም እንዲሁ።

ይህም ቡድኑ ከስልጣን ውጪ ለትግራይ ሕዝብ ጥቅም ዴንታ እንደሌለው በተግባር ያሳያል ነው ያሉት።

የሽብር ቡድኑ በትግራይ ላይ ሲፈጽም የቆየው ግፍ አልበቃ ብሎት “ትግራይ ነጻ ትወጣለች፤ ሀገረ ትግራይን እንመሰርታለን” የሚል የትግራይን ሕዝብ ለከፋ ችግር የሚዳርግ ትርክት እያሰራጨ መሆኑንም አንስተዋል። በመሆኑም የትግራይ ሕዝብ የሽብር ቡድኑን ሴራ ተገንዝቦ ለቡድኑ ተባባሪ ከመሆን እንዲቆጠብ ጥሪ አቅርበዋል።

“ቡድኑ መንግሥት ጋር ለድርድር መቅረብ አለብን” በሚል አጉል ሃሳብ ንጹሃን ላይ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችልም ጥንቃቄ መደረግ እንዳለት ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን በመጠበቅ የአሸባሪውን ቡድን ሴራ ማክሸፍ እንዳለባቸውም ነው የገለጹት። ዓለም አቀፉ ማኀረበረሰብም የሽብር ቡድኑ ላይ ተጽእኖ እንዲያደርግም ዶክተር አረጋዊ ጥሪ አቅርበዋል።

የሽብር ቡድኑ አባላት ልጆች በውጭ ሀገራት በድሎት እንደሚኖሩ ጠቁመው በመሆኑም በተሳሳተ መረጃ ከሽብር ቡድኑ ጎን የተሰለፉ የትግራይ ወጣቶች ከቡድኑ እራሳቸውን እንዲያገሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በትግራይ ክልል የተደረገው የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ በመስጠት መሆኑን መንግሥት መግለጹ ይታወቃል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

The post “አሸባሪው ህወሃት ከስልጣን ውጪ ለትግራይ ሕዝብ ጥቅምና ህልውና ዴንታ እንደሌለው በተግባር አሳይቷል” ዶክተር አረጋዊ በርሄ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

Trending Articles