Quantcast
Channel: The Habesha: Latest Ethiopian News, Analysis and Articles
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

“በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ያላትን ክብር የሚመጥን ውጤት ለማስመዝገብ ጠንካራ ዝግጅት ተደርጓል”የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ

$
0
0



“በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ያላትን ክብር የሚመጥን ውጤት ለማስመዝገብ ጠንካራ ዝግጅት ተደርጓል” የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ
ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 24/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የ2020 ቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ፣
የአትሌቲክስ፣ ወርልድ ቴኳንዶ እና ብስክሌት ፌደሬሽኖች በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ እንዳሉት ቶኪዮ በ1957 ዓ.ም ሻምበል አበበ ቢቂላ
በማራቶን ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያን የአሸናፊነት ምሳሌ የሆነ ድልን ያስመዘገበበት ልዩ ቦታ ነው። ይህንን ክብር
የሚመጥን ድልና ውጤት ለማስመዝገብም ጠንካራ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።
በመንግሥት ጭምር ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ ሕዝባዊ ድጋፍና መነቃቃት ለመፍጠር የኦሎምፒክ ችቦ በተለያዩ ከተሞች ተዟዙሮ
ድጋፍ አግኝተናል ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የክልል መንግሥታት እና የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የነበራቸው ድጋፍ ከፍተኛ
መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ለቶኪዮ የመጨረሻ ምዕራፍ ዝግጅት ላይ እንገኛለን ያሉት ዶክተር አሸብር ለሀገርና ለሕዝቡ የሚመጥን ውጤት ለማምጣት
ከሁሉም ፌደሬሽኖች ጋር በቅንጅት እየተሠራ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ቶኪዮ ላይ ከአትሌቲክስ በተጨማሪ በወርልድ ቴኳንዶ፣ በብስክሌትና ውኃ ዋና ስፖርት ትሳተፋለች።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኝ
ውጤታማ ሥራ ተሠርቷል ብለዋል።
ለቶኪዮ ዝግጅት የሆቴልና ሌሎች ወጭዎች ኦሎምፒክ ኮሚቴ መሸፈኑ በመግለጫው ተጠቅሷል። ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር የነበሩ
ልዩነቶች እንደተፈቱም ተገልጿል። ሌሎች ፌደሬሽኖችም በኦሎምፒክ ኮሚቴው ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንና
ከተሳትፎ የዘለለ ውጤት ለማስመዝገብ እየሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ወደ ቶኪዮ ለሚያመሩ ልኡካን ሐምሌ 10/2013 ዓ.ም የሽኝት ፕሮግራም ይኖራል ተብሏል። ውድድሩም ሐምሌ 16/2013
ዓ.ም እንደሚካሄድ ተመልክቷል፡፡
ዘጋቢ፡- ባዘዘው መኮንን – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m






Previous article“መከላከያ ሠራዊት ከትግራይ መውጣቱን ተከትሎ መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት በጎ ምላሽ መስጠት ጀምረዋል” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር


Source link

The post “በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ያላትን ክብር የሚመጥን ውጤት ለማስመዝገብ ጠንካራ ዝግጅት ተደርጓል” የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

Trending Articles