Quantcast
Channel: The Habesha: Latest Ethiopian News, Analysis and Articles
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

የጃፓን መንግስት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ለሆኑት አቶ ሆርዶፋ በቀለ የክብር ኒሻን አበረከተ

$
0
0
አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓን መንግስት የሚበረከተው እና የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ለማጠናከር አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የሚበረከተው የጃፓን መንግስት የክብር ኒሻን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ለሆኑት አቶ ሆርዶፋ በቀለ ተበርክቶላቸዋል።
የክብር ሽልማቱ በጃፓን መንግስት እድሜ ጠገቡ ሲሆን ÷ይህንን ሽልማት ከዚህ ቀደም ለኢኮኖሚ አማካሪ የነበሩት አቶ ነዋይ ገብረ አብ ፣ ዶክተር አርከበ ዕቁባይ እና ለቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተበርክቷል።
በዛሬው ዕለትም የጃፓን መንግስት ለካይዘን ፍልስፍና በኢትዮጵያ መተግበር ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ለሆኑት አቶ ሆርዶፋ በቀለ አበርክቷል።
በእውቅና መርሃ ግብሩም ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የምክር ቤቱ ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለን ጨምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ተገኝተዋል።
በመርሃ ግብሩም አቶ ሆርዶፋ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት እንዲጠናከር ለበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና ቀርቦላቸዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የጃፓን መንግስት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ለሆኑት አቶ ሆርዶፋ በቀለ የክብር ኒሻን አበረከተ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.



Source link

The post የጃፓን መንግስት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ለሆኑት አቶ ሆርዶፋ በቀለ የክብር ኒሻን አበረከተ appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

Trending Articles