Quantcast
Channel: The Habesha: Latest Ethiopian News, Analysis and Articles
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

በአማራ ክልል የሲሚንቶ እጥረትን ለመፍታት በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንደወሰዱ ተገለጸ፡፡

$
0
0

በአማራ ክልል የሲሚንቶ እጥረትን ለመፍታት በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንደወሰዱ ተገለጸ፡፡

ባሕር ዳር፡ ጥር 06/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከአምባሰል የንግድ ሥራዎች ድርጅት ጋር በመተባበር በሲሚንቶና ብረት ምርት አቅርቦት ዙሪያ ከአጋር አካላት ጋር ምክክር አካሂዷል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ አቶ ብርሃኑ ጣእምያለው እንደተናገሩት በሲሚንቶና በብረታ ብረት ምርት ላይ በየጊዜው እየታየ ያለውን የዋጋ ጭማሪ እና ፍትሃዊነት የጎደለው ስርጭት የግንባታ ዘርፉን እየተፈታተነው በመሆኑ ማስቆም ይገባል፡፡

እንደ ኀላፊው ገለጻ የግንባታ ዘርፉ ለሀገራችንም ሆነ ለክልላችን ኢኮኖሚ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ እድል መፍጠሪያ ዘርፍም ነው፡፡ ለዚህ ዘርፍ ግብዓት የሚሆነው የሲሚንቶ ምርት ከፋብሪካዎች ጀምሮ እስከ ተጠቃሚው ለማድረስ ከአላስፈላጊ የግብይት ስርዓት ነጻ ሆኖ መቅረብ አለበት ነው ያሉት፡፡ ባለድርሻ አካላት በአንድ በኩል አቅርቦቱ የሚሻሻልበትን በሌላ በኩል ደግሞ ግብይቱ በፍትሃዊነት እንዲደርስ ሊሠሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በብረትና በሲሚንቶ ግብይት ላይ የሚታየውን ህገ ወጥ ንግድ ለማስቆም የፋብሪካዎችን የማምረት መጠን ወደ 85 በመቶ ማድረስ አለመቻሉ፣ በሲሚንቶ አቅርቦትና ስርጭት ዙሪያ የተዘጋጀውን የማስፈጸሚያ መመሪያ ተግባራዊ አለማድረግ እና የሲሚንቶ አቅራቢ ወኪሎች ከፋብሪካ የወሰዱትን ሲሚንቶ ለማን እንደሸጡት መረጃ እንዲያቀርቡ አለማድረግ ለችግሩ መባባስ ዋነኞቹ ናቸው ተብሏል፡፡

የኬሚካልና የግንባታ ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል አላላ በበኩላቸው በ2012 ዓ.ም በሀገር ደረጃ 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ የተመረተበት ዓመት ቢሆንም እጥረት ተፈጥረዋል ብለዋል፡፡ ለችግሩ መፈጠር ደግሞ በሃገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ የግንባታ ሥራዎች እድገት መኖሩ እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል፡፡

ችግሩን ለመፍታት መንግሥት ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች ማስፋፊያ ቦታዎችን መፍቀድ፣ ወደ ዘርፉ የሚመጡ አዳዲስ ባለሃብቶችን ማበረታታትና የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ማመቻቸት እንደሚገባ ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ገበያ ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ እሸቴ አስፋው በሲሚንቶና በብረታ ብረት ግብይት ላይ በየጊዜው የሚታየውን የዋጋ መጨመር ለማስተካከል እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዘርፉ ያለውን እጥረት መፍትሄ እንዲያገኝ ፋብሪካዎች ያለባቸውን የኀይል እጥረት መቅረፍ፣ የሚጠቀሙትን የድንጋይ ከሰል ምርት መጠኑን ማሳደግና መሰል ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡ ለዚህም በሥራ ላይ ያሉ ፋብሪካዎችን በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ ማድረግና የማምረት አቅማቸው 85 በመቶ እንዲደርሱ እየተሠራ እንደሚገኝ አቶ እሸቴ ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል ብቻ የሲሚንቶ እጥረትን ለመፍታት በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውንም አስታውቀዋል፡፡ ፋብሪካዎች ያመረቱትን ምርት ለተጠቃሚው ለማድረስ የሚያስችሉ የግብይት ሂደቶችን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ በዘርፉ የሚሳተፉ፣ የሚመሩ እና የጸጥታ አካላት ችግሩን ለመቅረፍ ተባባሪ ሊሆኑ እንደሚገባል ተገልጿል፡፡

ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

The post በአማራ ክልል የሲሚንቶ እጥረትን ለመፍታት በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንደወሰዱ ተገለጸ፡፡ appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

Trending Articles