Quantcast
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13088

“በክልሉ 75 የሚደርሱ የግብርና ግብዓት እና አገልግሎት ማዕከላት ተቋቁመው አገልግሎት እየሠጡ ነው”የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ




Image may be NSFW.
Clik here to view.

“በክልሉ 75 የሚደርሱ የግብርና ግብዓት እና አገልግሎት ማዕከላት ተቋቁመው አገልግሎት እየሠጡ ነው” የአማራ ክልል
ግብርና ቢሮ
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ በዘር ለመሸፈን እየተሠራ
ነው፡፡ በ2013/2014 የመኸር እርሻ ከ131 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት መታቀዱን ከክልሉ ግብርና ቢሮ
የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
በክልሉ ከግብርና ግብዓት አቅርቦትና ሥርጭት አኳያ ያሉ ችግሮችን መፍትሔ መስጠት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አበጀ ስንሻው በክልሉ ሰፊ የሚለማ መሬት እና የሰው ኀይል ቢኖርም እየለማ
ያለው መሬት በሚጠበቀው ልክ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ አቶ አበጀ እንዳሉት በክልሉ 75 የሚደርሱ የግብርና ግብዓት እና
አገልግሎት ማዕከላት ተቋቁመው አገልግሎት እየሠጡ ነው፡፡ እነዚህ ማዕከላት የሚሠጡት አገልግሎት አናሳ በመሆኑ በጋራ
አቅማቸውን አሰባስበው አክሲዮን በመመስረት የተሻለ ሥራ እንዲሠሩ በተደረገላቸው ድጋፍ መሠረት 35 ማዕከላት በጋራ ፈለገ
ግዮን የግብርና ግብዓት እና ውጤቶች አስመጭና ላኪ አክሲዮን ማኅበርን መመስረት ችለዋል ብለዋል፡፡ አክሲዮን ማኅበሩ
በመንግሥት ብቻ ይሸፈን የነበረውን የግብርና ግብዓት የማቅረብ ሥራም ይሠራል ብለዋል፡፡
አክሲዮን ማኅበሩ በዓለም ተወዳዳሪ አስመጭና ላኪ በመሆን የአርሶ አደሮችን የግብዓት ፍላጎት በማሟላት አርሶ አደሮች
ከራሳቸው አልፈው ለዓለም ገበያ እንዲያመርቱ የራሱን አስተዋጽኦ በብቃት ማበርከት እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡
የፈለገ ግዮን የግብርና ግብዓትና ውጤቶች አስመጭና ላኪ አክሲዮን ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ባለው ወንድሙ በተናጠል
የነበረውን የግብርና ግብዓት አቅርቦት ወደ አንድ በማምጣት ጥራት ያላቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የአርሶ
አደሮችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንሠራለን ብለዋል፡፡
አክሲዮን ማኅበሩ ሙሉ በሙሉ ወደሥራ ሲገባ የግብርና ግብዓት በበቂ ሁኔታ በማስገባት ለአርሶ አደሩ ያቀርባል፤ የተመረተውን
ምርት ወደ ውጭ በመላክ ሀገሪቱ በቂ የውጪ ምንዛሬ እንድታገኝ ያስችላል ነው ያሉት፡፡
“አርሶ አደሮች ከእለት ፍጆታ አልፎ ለሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች ግብዓት የሚውል ምርት የሚያመርቱበትን መንገድ ማመቻቸት፤
ግብርናው ከባህላዊው አስተራረስ ወጥቶ በዘመናዊ መንገድ የሚመረትበትን አሠራር መፍጠር ዋነኛ ተግባራችን ይሆናል”
ብለዋል፡፡
ለሥራው ስኬታማነት የክልሉ ግብርና ቢሮ፣ ግብርና ሚኒስቴር እና የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ተገቢውን የፋይናንስ እና
የእውቀት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
ፈለገ ግዮን የግብርና ግብዓት አቅርቦት እና ውጤቶች አስመጭና ላኪ አክስዮን ማኅበር ተመስርቶ እውቅና ተሠጥቶታል፡፡
ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m






Previous articleየኢትዮጵያና ህንድን የኢንዱስትሪ ልማትና የንግድ ግንኙነት ለማጎልበት የሚያስችል ምክክር ተካሄደ፡፡


Source link

The post “በክልሉ 75 የሚደርሱ የግብርና ግብዓት እና አገልግሎት ማዕከላት ተቋቁመው አገልግሎት እየሠጡ ነው” የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13088

Trending Articles