Quantcast
Channel: Ethiopian News: Trusted, In-Depth Analysis | The Habesha
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13074

የአዉሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

$
0
0

የአዉሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ከህብረቱ በድጋፍ የተገኙት የህክምና ቁሳቁስ የወረርሽኙ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባቸዉ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተደራሽ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

የአዉሮፓ ህብረትን ወክለዉ የድጋፍ ቁሳቁሱን ያስረከቡት ሄሪክ የኮሮና ቫይረስ አሁን በሁሉም የዓለም ሀገራት የጤናዉን ዘረፍ እየፈተነ ያለ ችግር ነው ብለዋል፡፡
የአዉሮፓ ህብረት ወረርሽኙ እያደረሰ ያለዉን ተጽዕኖ ለመቀነስ ከ22 ቢሊዮን ዩሮ በላይ መድቦ እየሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ እየፈተነ የሚገኘውን ወረርሽኝ ለመከላከል የአዉሮፓ ህብረት ከዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ጋር በመሆን እየሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

ወረርሽኙ በጤና እና ምጣኔ ሀብት ላይ የሚያደርሰዉን ችግር ለመቋቋም ከተመደበው ከ22 ቢሊዮን ዩሮ ዉስጥ 767 ሚሊዮን ዩሮ የሚሆነዉ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የተመደበ ነዉም ተብሏል፡፡ ከዚህ ውስጥም 24 ቢሊዮን ብር የሚሆነዉ ገንዘብ ለኢትዮጵያ የሚሰጥ ነዉ፡፡

የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶክተር) የቅንጅታዊ አሠራርን አስፈላጊነት ወሳኝ መሆኑን አንሰተዋል፡፡

የተደረገው ድጋፍ ወረርሽኙን ለመካላከል የሚያግዝ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ድጋፉን ላደረገው የአዉሮፓ ህብረትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዋና ጸሐፊው የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር ዉጤታማ አሠራርን አድንቀዋል፡፡

የወረርሽኙን ስርጭት በመግታት በኩል የሁሉም ልማት አጋሮች እና የሚመለከታቸዉ አካላት የተቀናጀ ሥራን የሚጠየቅበት ወቅት ላይ እንገኛለን ነው ያሉት፡፡ አሁን እያደረግነዉ ያለነዉ የመደጋገፍ ተግባርም ዉጤታማ እንደሚያደርገን አልጠራጠርም ብለዋል፡፡

ለኢትዮጵያ የተደረገዉ ድጋፍ ለበሽታዉ ተጋላጭ ለሆኑ አካባቢዎች ጠቃሜታዉ የጎላ መሆኑን ነው ያነሱት፡፡

የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ደጉማ ስለ ድጋፉ የአዉሮፓ ህብረትን እና ኢጋድን አመስግነዋል፡፡

ወረርሽኙ እንደ ኢትዮጵያ ታዳጊ ለሆኑ ሀገራት የሚያሳድረዉ ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው ያሉት ዶክተር ደረጀ ድጋፉ ወቅታዊ እና አስፈላጊነቱን ያጎላዋል ብለዋል፡፡ ወረርሽኙ እያደረሰ ያለዉ ችግር ጤና ላይ ብቻ አለመሆኑንም አንስተዋል፡፡
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የወረርሽኙ ስርጭት በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነዉም ብለዋል፡፡ የበሽታዉን ስርጭት ለመግታት ከልማት አጋሮች ጋር እየሰሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ 8 አምቡላንሶች፣ 19 የቫይረሱ መመርመሪያ መሳሪያዎች፣ 500 ሺህ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎችና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

ዘጋቢ:– ራሄል ደምሰው– ከአዲስ አበባ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Source link

The post የአዉሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13074

Trending Articles