
“ተፎካካሪ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙኃን የተመደበላቸውን የአየር ሰዓት በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይገባል” የምርጫ ቦርድ ምክትል
ሰብሳቢ ውብሸት አየለ
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን
የምርጫ ቅስቀሣ ነጻ የአየር ሰዓት እና የጋዜጦች አምድ ድልድል አስተዳደር ሥርዓትን ዛሬ በይፋ አካሂደዋል። በ6ኛው ሀገራዊ
ምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአየር ሰዓት ድልድል እጣቸውን አውጥተዋል።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ “ተፎካካሪ ፓርቲዎች የተመደበላቸውን የአየር ሰዓት የፓለቲካ
ኘሮግራም ትውውቅ እና ማኒፌስቷቸውን ለመራጩ በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ ይገባል” ነው ያሉት።
ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳን በጨዋነት እና የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ታሣቢ ባደረገ መልኩ በኀላፊነት እንዲጠቀሙበትም
ጠይቀዋል።
መገናኛ ብዙኃን የተደለደለውን የአየር ሰዓት ከአድሏዊነት እና ከወገንተኝነት ነፃ በሆነ መልኩ ማገልገል እንደሚገባቸው
ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሙሀመድ ኢድሪስ 620 ሰዓት የራዲዬ፣ 425 የቴሌቪዥን አየር ሰዓት
እንዲሁም 615 የጋዜጣ አምድ ለፓርቲዋች ቅስቀሳ መደልደሉን ገልጸዋል፡፡
ፓርቲዎች የተደለደለውን አምድና አየር ሰዓት በኀላፊነት እና በብቃት እንዲጠቀሙበት ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ቅስቀሳ 21 ራዲዬ ጣቢያዎች፣ 23 ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እና
8 ጋዜጦች አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጿል።
ፓርቲዎቹ የአየር ሰዓት ድርሻቸውን ባላቸው የዕጩ ብዛት፣ በሴት ዕጩዎች ብዛት፤ በአካል ጉዳተኛ ዕጩ ብዛት እና ሌሎች ዝርዝር
መስፈርቶች መስረት ተደርጎ እንደተደለደለ ተመላክቷል፡፡
ዘጋቢ፡- ኃይለኢየሱስ አለልኝ- ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
The post “ተፎካካሪ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙኃን የተመደበላቸውን የአየር ሰዓት በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይገባል” የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.