
የአማራና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች በልማት እና በሰላም ጉዳዮች ላይ በጋራ እየመከሩ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች በሁለቱ
ክልሎች የጋራ ሠላም እና የልማት አጀንዳዎች ላይ እየመከሩ ነዉ፡፡
በምክክር መድረኩ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች በተደጋጋሚ የሚከሰቱ የሰላም እና የጸጥታ ችግሮችን ተቀናጅቶ ለመከላከል
በትብብር መሥራት የሚቻልበትን ሁኔታ መፍጠር ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡
በሁለቱም ክልሎች የሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን ተከትሎ በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለዉን ሞትና መፈናቀል በፍጥነት
ማስቆም፣ የግጭቱ ጠንሳሾች እና ተዋናዮች ላይ አስፈላጊዉን እርምጃ መዉሰድ፣ በተከሰቱ ግጭቶች ጉዳት የደረሰባቸዉ ወገኖች
ፍትሕ እንዲያገኙ እና ወንጀለኞች ለሕግ እንዲቀረቡ ማድረግ፣ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው በፍጥነት መመለስና ማቋቋም
እንዲሁም በክልሎቹ ዘላቂ ሰላም ከማስፈን አኳያ በትብብር ለመሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሁለቱ ክልሎች አመራሮች
በመወያየት ላይ ይገኛሉ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የኦሮሞ እና የአማራ ወንድማማች ሕዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ትስስርና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማጠናከር፣
አጎራባች ዞኖች ላይ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ግጭቶችን በተቀናጀ ሁኔታ መከላከል፣ በሁለቱ ክልሎች መካከል እየተሠሩ ያሉ
የመሰረተ ልማት ሥራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የዉይይቱ አንኳር ጉዳዮች ናቸዉ፡፡
በመድረኩ የሁለቱም ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር
አገኘሁ ተሻገር እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በጋራ እየመሩት ነዉ፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
The post የአማራና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች በልማት እና በሰላም ጉዳዮች ላይ በጋራ እየመከሩ ነው፡፡ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.