Quantcast
Channel: The Habesha: Latest Ethiopian News, Analysis and Articles
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

የነዳጅ እጥረትን ለመፍታት የነዳጅ አቅርቦትን መጨመርና ሕገ ወጥነትን መቆጣጠር እንደሚገባ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ገለጹ፡፡

$
0
0

የነዳጅ እጥረትን ለመፍታት የነዳጅ አቅርቦትን መጨመርና ሕገ ወጥነትን መቆጣጠር እንደሚገባ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ገለጹ፡፡

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 21/2013 ዓ.ም (አብመድ) በአማራ ክልል የሚታየውን የነዳጅ አቅርቦት ችግር ለመፍታትና ሕገወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ትኩረት ያደረገ ውይይት በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል። በውይይቱ ከአማራ ክልል ከሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የሥራ ኀላፊዎችና የነዳጅ ማደያ ባለሃብቶች ተገኝተዋል፡፡

ወይዘሮ ወርቃዓለም ኀይለሚካኤል ከደቡብ ወሎ ዞን ጀማ ወረዳ በውይይቱ የተገኙ ባለሃብት ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት በነዳጅ ንግድ ዘርፍ መሰማራት ውጤታማ እያደረጋቸው አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ ትርፋማ እንዳይሆኑ ደግሞ የገበያ ሥርዓትና የአቅርቦት ችግሮችን በዋናነት ጠቅሰዋል፡፡ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርገው ከሚያስገቡት ነዳጅ በሊትር 0.236 ሳንቲም ብቻ አትርፈው እንደሚሸጡም ተናግረዋል፡፡ ይህም የሰራተኞችን ደሞዝ ለመሸፈን እንኳን እንደሚያስቸግራቸው ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም መንግሥት በነዳጅ ዘርፉ ለተሠማሩ ባለሃብቶች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡ በክልሉ የሚታየውን የነዳጅ እጥረት ችግር ለመፍታት የነዳጅ አቅርቦትን መጨመርና ሕገ ወጥነትን መቆጣጠር እንደሚገባም ጠቅሰዋል፡፡

ከሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ በውይይቱ የተሳተፉት ባለሃብት አምሳሉ ብርሃኑ ደግሞ የማደያ ሥራ በጣም አነሰተኛ ትርፍ የሚገኝበት በመሆኑ በዘርፉ የተሠማሩ ዜጎች ወደ ጥቁር ገበያ ንግድ እንዲገቡ እያስገደዳቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በነዚህ ችግሮች ውስጥም ቢሆን ከትርፍ ይልቅ ሕዝብን ለማገልገል በታማኝነት እየሠሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይ መንግሥትም ለነዳጅ ማደያዎች የቦታ ድጋፍ ማድረግ፣ የነዳጅ ጫኝ ተሸከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ ሆነው የሚገቡበትን አሠራር ማመቻቸትና የንግዱ ሥርዓት ዘመናዊ የሚሆንበትን መንገድ መፈለግ አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ተዋቸው ወርቁ ከነዳጅ አቅርቦት ጋር ያለው ችግር ሀገራዊ ቢሆንም በክልሉ የተረጋጋ የነዳጅ የግብይት ሥርዓት እንዲፈጠር ከፌዴራል መንግሥት ጋር እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

የነዳጅ መሸጫ ዋጋም በመንግሥት የተመን ዋጋ የተቀመጠ በመሆኑ የትርፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እንደ አቶ ተዋቸው መረጃ ሕገ ወጦችን ለመቆጣጠር ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተሠራው ሥራ፡-

• 150 ሺህ 491 ሊትር ነዳጅ በሕግ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተይዟል

• 7 ማደያዎች ታሽገው ችግራቸውን ሲያስተካክሉ እንዲከፈቱ ተወስኗል

• 8 ማደያዎች በጥቁር ገበያ ነዳጅ ሲሸጡ ተይዘው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደርጓል

• 35 ማደያዎች የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በክልሉም 212 የነዳጅ ማደያዎችና 107 ሺህ 200 ተሽከርካሪዎች እንደሚገኙም አቶ ተዋቸው ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

The post የነዳጅ እጥረትን ለመፍታት የነዳጅ አቅርቦትን መጨመርና ሕገ ወጥነትን መቆጣጠር እንደሚገባ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ገለጹ፡፡ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

Trending Articles