Quantcast
Channel: The Habesha: Latest Ethiopian News, Analysis and Articles
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

በመጪው ምርጫ ሊተኮርበት የሚገባው ሰው ወጥቶ እንዳይመርጥና ደህንነት እንዳይሰማው የሚያደርጉ ቅጥረኞች ጉዳይ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

$
0
0
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጪው ምርጫ የከተማዎች ሰላማዊነት እንደማያሳስብ እና በመጪው ምርጫ ሊተኮርበት የሚገባው ሰው ወጥቶ እንዳይመርጥና ደህንነት እንዳይሰማው የሚያደርጉ ቅጥረኞች ጉዳይ መሆኑን ተናገሩ፡፡
በአዲስ ወግ የውይይት መድረክ ላይ የተሳተፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመጪው ምርጫ የከተማዎች ሰላማዊነት አያሳስብም ያሉ ሲሆን ሊተኮርበት የሚገባው ሰው ወጥቶ ለመምረጥ ሕዝብ ደህንነት እንዳይሰማው የሚያደርጉ ቅጥረኞች ጉዳይ ነው ብለዋል።
ይህንንም በጊዜ ለጸጥታ አካላት መረጃ በመስጠት ለመከላከል እንችላለን ነው ያሉት።
“መጪው ምርጫ ዕድል እና ችግሮችን ይዟል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለቱንም ተገንዝቦ ለመምረጥ የሚነሳና የሚመርጠውን አካል ሕጋዊነት ያረጋገጠ ማኅበረሰብ እንዲፈጠር ይህን መሰል ውይይቶች ያስፈልጋሉ ብለዋል።
አጋጣሚውን ሁከት መቅስቆሻ ለማድረግ የሚፈልጉም ቅጥረኞች መኖራቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ችግሮችን ፈርተው ምርጫ አሁን አይኑር የሚሉም አካላት መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡
የእኛ ዓላማ ኢትዮጵያን አሸናፊ ማድረግ ነውና ሁላችን ኢትዮጵያውያን ለዚያ እንተባበር ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
እንዲሁም በዚህ ምርጫ ካለፉት የተሻለ ውጤት ይገኛል ብለው እንደሚያምኑ በውይይቱ መናገራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በመጪው ምርጫ ሊተኮርበት የሚገባው ሰው ወጥቶ እንዳይመርጥና ደህንነት እንዳይሰማው የሚያደርጉ ቅጥረኞች ጉዳይ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.



Source link

The post በመጪው ምርጫ ሊተኮርበት የሚገባው ሰው ወጥቶ እንዳይመርጥና ደህንነት እንዳይሰማው የሚያደርጉ ቅጥረኞች ጉዳይ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

Trending Articles