
“ሕዝባችን በጎርፍና በነፋስ ሳይሸበር ተረፈ ትህነግን አሸንፈን እንደምንሻገር ቅንጣት ያህል ጥርጥር የለኝም፤ ለ6ኛው ሀገራዊ
ምርጫ ለሕዝብ የቆሙ እጩዎችን ይዘን ቀርበናል” የአማራ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አብርሐም አለኸኝ
ባሕር ዳር: መጋቢት 19/2013 ዓ.ም(አብመድ) የአማራ ብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃግብር በባሕር ዳር
ተካሂዷል።
በመርኃ ግብሩ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቀሰሙ
ማሞ፣ የብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም፣ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አብርሐም አለኸኝን
ጨምሮ የፓርቲው ከፍተኛ መሪዎችና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።
የአማራ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አብርሐም አለኸኝ እንዳሉት ወቅቱ የአማራ ሕዝብ በማንነቱ እየተጠቃ ያለበት የፖለቲካ
ትርፍ ለማግኘት የሚፍጨረጨሩ ኀይሎች በየአቅጣጫው ሕዝብ የሚያምሱበት ነው። እኛ አንገታችንን ለማስደፋት የሚሠሩ
በግፉዓን የሰከሩ ኀይሎችን ልክ የምናስገባበት ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለንም ብለዋል።
“ሕዝባችን በጎርፍና በነፋስ ሳይሸበር ተረፈ ትህነግን አሸንፈን እንደምንሻገር ቅንጣት ያህል ጥርጥር የለኝም፤ ለ6ኛው ሀገራዊ
ምርጫ ለሕዝብ የቆሙ እጩዎችን ይዘን ቀርበናል” ነው ያሉት።
ከስሜታዊነትና ሥርዓት አልበኝነት ወጥተን መንቀሳቀስ አለብን፤ምርጫችን ከአማራ ሕዝብ ክብር በታች ነው፤ የሕዝብን ድምጽ
ለማክበር ዝግጁ መሆን አለብን ሲሉም ለፓርቲያቸው ደጋፊዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም በበኩላቸው ሕዝቡ ምርጫን
የስጋት መገለጫ ሳይሆን በነጻነት የሚያስተዳድረውን ፓርቲ እንዲመርጥ የሚያስችለው አድርጎ እንዲያስብ ምቹ ሁኔታዎችን
መፍጠር አለብን ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ 6ኛው ሐገራዊ ምርጫ ነጻና ሰላማዊ ኹኖ እንዲከናወን ይሠራል፤ ሕዝቡ ለሀገር ህልውና ይበጃል የሚለውን
የፓለቲካ ፓርቲ መርምሮ ይምረጥ፤እኛን ከመረጡን በንግግር ሳይሆን በተግባር ሃሳባችንን ለመፈጸም ቁርጠኛ ነን ሲሉ
ተናግረዋል።
ሁሉም የተፎካካሪ ፓርቲዎች የሀሳብ መለያየት ማለት ጠላትነት አለመሆኑን በመገንዘብ የሕዝብን ድምጽ በጸጋ መቀበል
እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 138 እና ለክልል ምክር ቤት ደግሞ 294
እጩዎችን ማቅረቡን አስታውቋል።
ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቀረቡት 138 እጩዎች መካከል ከአንዱ በስተቀር ሁሉም አዲስ ናቸው ተብሏል።
ለክልል ምክር ቤት ከቀረቡት እጩዎች 5 በመቶዎች ብቻ ነባር ናቸው።
እጩዎቹ በትምህርት ዝግጅታቸው የተሻሉና ለሕዝብ ጥቅም የቆሙ መሆናቸውንም ፓርቲው ገልጿል።
ዘጋቢ:- ስማቸው እሸቴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
The post “ሕዝባችን በጎርፍና በነፋስ ሳይሸበር ተረፈ ትህነግን አሸንፈን እንደምንሻገር ቅንጣት ያህል ጥርጥር የለኝም፤ ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለሕዝብ የቆሙ እጩዎችን ይዘን ቀርበናል” የአማራ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አብርሐም አለኸኝ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.