Quantcast
Channel: The Habesha: Latest Ethiopian News, Analysis and Articles
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

በሀገሪቱ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የመራጮች ስልጠና ለመስጠትና ቁሳቁስ ለማጓጓዝ እንዳልቻለ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ገለጸ፡፡

$
0
0


በሀገሪቱ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የመራጮች ስልጠና ለመስጠትና ቁሳቁስ ለማጓጓዝ እንዳልቻለ የኢትዮጵያ ምርጫ
ቦርድ ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 18/2013 ዓ.ም (አብመድ) የየሳምንቱን ተግባርና እንቅስቃሴውን ለፓርቲዎች እያሳወቀ ያለው የኢትዮጵያ
ምርጫ ቦርድ በሳምንቱ የምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠናን በተመለከተ ገለጻ አድርጓል።
የተሰጡ ስልጠናዎችን በተመለከተ እስካሁን በሁለት ዙር 20 መሪ አሰልጣኞችን እና 200 ዋና አሰልጣኞችን፣ 3ሺህ 500
የመስክ አሰልጣኞችን፣150 ሺህ የምርጫ ጣቢያ የምርጫ አስፈፃሚዎችን እና 100 ሺህ የሚጠጉ የምርጫ ጣቢያ ምርጫ
አስፈፃሚዎችን አሰልጥኖ የመራጮች ምዝገባ እንዲያከናውኑ ማሰማራቱን ቦርዱ በመግለጫው አመልክቷል፡፡
ሆኖም ቦርዱ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንዳንድ አካባቢዎች፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በአፋር፣ በሶማሌና በኦሮሚያ
ክልል ወለጋ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች እስካሁን የመራጮች ስልጠና መስጠትና ቁሳቁስ ማጓጓዝ አልቻልኩም ብሏል።
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የኦንላይን የመራጮች መመዝገቢያ ቅጽ ተዘጋጅቷል ያለው ምርጫ ቦርድ ተማሪዎች በመራጮች ምዝገባ
ወቅት ትምህርት ላይ መሆናቸውን ታሳቢ በማድረግ ባሉበት ቦታ ሆነው መመዝገብ እንዲችሉ ይህን የቴክኖሎጂ ምዝገባ
ማዘጋጀቱን ገልጿል።
ተማሪዎች የሞሉት መረጃም በራሳቸው የይለፍ ቃል ብቻ መግባት የሚያስችል በመሆኑ ደኀንነቱ የተጠበቀ ነው ብሏል ቦርዱ።
መመዝገቢያው የተዘጋጀው በአማርኛና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ በሌሎች ቋንቋዎችም ለማዘጋጀት ቦርዱ
እንደማይቸገር ገልጿል።
ዘገቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ -ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m




Previous articleʺፍቅርን በጀጎል ውስጥ አየኋት”
Next articleጥቃቱ ቆሞ ሰላም እንዲፈጠር የጸጥታ አስከባሪ አካላት ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ በአጣዬ ከተማ ከጥፋቱ የተረፉ ተጎጂዎች ጠየቁ፡፡

Source link

The post በሀገሪቱ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የመራጮች ስልጠና ለመስጠትና ቁሳቁስ ለማጓጓዝ እንዳልቻለ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ገለጸ፡፡ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

Trending Articles