Quantcast
Channel: The Habesha: Latest Ethiopian News, Analysis and Articles
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

በመዲናዋ የተገነቡ የቀዳማይ ልጅነት እድገት ፕሮግራም የህጻናት መንከባከቢያ ማዕከላት ተመረቁ

$
0
0

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በከተማዋ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የቀዳማይ ልጅነት እድገት ፕሮግራም የህጻናት መንከባከቢያ ማዕከላትን በይፋ ስራ አስጀመሩ።

ማዕከላቱ በከተማዋ ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በተጋለጡ ቤተሰቦች ውስጥ የሚገኙ ሕጻናትን የሚንከባከብ ነው ተብሏል፡፡

በዚህ ወቅትም የከተማ አስተዳደሩ ብሩህ አዕምሮና መልካም ስብዕና ያላቸውን ዜጎች ለማፍራት በሚደረገው ጥረት የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተጠቁሟል ።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከአትሌት መሠረት ደፋር እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በቀዳማይ የልጅነት ዕድገት ፕሮግራም በሕጻናት ስም የተሠየመውን አደባባይ አስመርቀዋል ።
በክፍለ ከተማው ህፃናት በእድሜያቸው የሚያነቡበት የህፃናት ቤተ መጽሐፍት የተገነባ ሲሆን፥ ህጻናት እየተጫወቱ የሚማሩበት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ከዚህ ባለፈም ህፃናት ለመታከም በሚመጡበት ወቅት እየተጫወቱ የሚታከሙበት ጤና ጣቢያም ተመርቋል።

በተጨማሪም መክፈል የማይችሉ እናቶች በተለይ የመንግስት ሰራተኞች ስራ ሲውሉ ልጆቻቸውን የሚያቆዩበት የህጻናት ማቆያ እንዲሁም ቆሬ የህፃናት አደባባይ ቅዳሜና እሁድ ሙሉ በሙሉ መንገዱን በመዝጋት ህፃናት በነፃ የሚጫወቱበት ዘመናዊ መጫወቻ በዛሬው እለት በይፋ ተመርቀዋል ።

የቀዳማይ ልጅነት እድገት ፕሮግራም እስከ 6 ዓመት ያሉ ህጻናት ጤንነታቸው እንዲጠበቅ፣ ስብዕና እና ሞራል እንዲገነባ የሚያደርግ ሲሆን ቀጣዩን ትውልድ ብቁ ዜጋ አድርጎ ከመቅረጽ አንጻር ፋይዳው የጎላ ነው መባሉን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!



Source link

The post በመዲናዋ የተገነቡ የቀዳማይ ልጅነት እድገት ፕሮግራም የህጻናት መንከባከቢያ ማዕከላት ተመረቁ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

Trending Articles