Quantcast
Channel: The Habesha: Latest Ethiopian News, Analysis and Articles
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

“የአማራ ልዩ ኀይል ትክክለኛ ኅብረ-ብሔራዊነትን በተግባር ያረጋገጠ ነው።”የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳዳሪ

$
0
0

“የአማራ ልዩ ኀይል ትክክለኛ ኅብረ-ብሔራዊነትን በተግባር ያረጋገጠ ነው።” የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳዳሪ

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 17/2013 ዓ.ም (አብመድ) የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳዳር ዋና አስተዳዳሪ አቶ በሪሁን ኪዳነማርያም ከባዱ ስጦታ ህይወትን አሳልፎ መስጠት ነው፤ የአማራ ልዩ ኀይልም ይህን ውድ ስጦታ አድርጎልናል ብለዋል፡፡ ዋና አስተዳዳሪው “እኛ ስንተኛ ቆሞ፤ ስንነቃም ቆሞ፤ እኛ ሲያምርብን እሱ ጠውልጎ፤ በጫካ በዱሩ እና በፀሐይ በቁሩ ከሰው እንዳልተፈጠረ መላ አካላቱ አይሆኑት ሆኖ ለህዝቡ እና ለእናት ሀገሩ የተሰዋን ማድነቅ እና ከጎኑ መሆን የራስን ሕይወትና ሀገርን የመታደግ ጉዳይ ነው” ብለዋል፡፡

ከፍ ባለ ሀገር የተገኘን ከፍ ያለ ሕዝብ ዘርም ነን ሲሉ የተናገሩት አቶ በሪሁን በአማራ ልዩ ኀይል ላይ የሚደረጉ ክፉ ሀሳቦች ትክክል እንዳልሆኑ አብራርተዋል።

ከመከላከያ እና ከሚሊሻ ጋር በመሆን ለኢትዮጵያችን መስዋእትነት የከፈለ እና እየከፈለ የሚገኝ ኀይል እንዴት በኢትዮጵያዊ ጀብዱ ሥራው አፈር ይነሰነስበታል? ያሉት አቶ በሪሁን ድርጊቱ አሳፋሪም አስነዋሪም እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በአማራ ልዩ ኀይል ላይ እየተዘመተ ያለው የአፍራሽ ሃሳብ ዘመቻ ክፉነት የተጫነው ስለሆነ ሊታረም ይገባል ሲሉ ኮንነዋል። ጁንታው ቢሳካለት ኑሮ ኢትዮጵያን የማፍረስ ዓለማ ነበረው ያሉት አቶ በሪሁን ሳይሳካ የቀረውም በአማራ ልዩ ኀይል፣ በሚሊሻና በመከላከያ እንዲሁም ኢትዮጵያውያን በጋራ በወንድማማችነት ስለቆሙ ነው ያሉት፡፡

“ልዩ ኀይላችን በየቦታው ደራሽ ለኢትዮጵያ አለኝታ ነው፤ ሁሌም ክብር ሊሰጠው ይገባል” ብለዋል፡፡ “ኢትዮጵያ የሁላችንም ሀገር ናት፤ የምትገነባውም በእውነተኛ ኅብረብሔራዊ ፌዴራሊዝም ስርዓትና በወንድማማችነት መሰረት ላይ ነው” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። መረጃው የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Source link

The post “የአማራ ልዩ ኀይል ትክክለኛ ኅብረ-ብሔራዊነትን በተግባር ያረጋገጠ ነው።” የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳዳሪ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

Trending Articles