Quantcast
Channel: The Habesha: Latest Ethiopian News, Analysis and Articles
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

$
0
0

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ሌሎችም የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት ነው መግለጫው የሰጠው፡፡

በመግለጫው የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ዝግጅትን፣ 50ኛ ዓመት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል አከባበር እንዲሁም ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር ስላለው አለመግባባት ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

ጋዜጣዊ መግለጫው የቶኪዮ 2020 ዝግጅትን የተመለከተውና እየተንከባለለ ስለመጣውና ሊቀረፍ ስላልቻለው ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር ያለው ቅራኔም ዋነኛው ስለመሆኑም ተገልጿል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉና ሌሎች በመድረኩ የነበሩት አባላት አፅንኦት ሰጥተው ሲናገሩ የነበረው “ለቶኪዮ 2020 ዝግጅት አትሌቶች ሆቴል መግባታቸው የሚታወቅ ቢሆንም አትሌቶች በወቅቱ ሊሟላላቸው የሚገቡና የስልጠናው ዋና አካል የሆኑ መሠረታዊ ግብአቶችና አለመሟላት አንስተዋል፡፡

የአሰራር ክፍተቶች ከመፍታት ይልቅ ችግሮች እየተባባሱ በመሄዳቸው እና ይህ ጉዳይ ደግሞ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተጎጂ እየሆኑ ያሉት አትሌቶችና አሰልጣኞች መሆናቸውም ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከዚህ በፊት በፌዴሬሽኑ ስራ ጣልቃ እንዳይገባና የአለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ መተዳደሪያ ደንብን እንዲያከብር መጠየቁን አስታውሰዋ፡፡

ሆኖም “ችግሩን ከመቅረፍ ይልቅ ጫና እየፈጠረብን በመምጣቱና” ይህም በአትሌቶቻችንና አሰልጣኞቻችን ላይም ችግሩ እየከፋ በመሄዱ የሚመለከተው አካል፣ መንግስትና ባለድርሻ አካላት ፌዴሬሽኑ በኦሎምፒክ ኮሚቴው ከመስመር የወጣ አሰራር ምክንያት እየደረሰበት ያለውን ችግር የመንግስት አካላትና ህዝብ እንዲያውቅልን እንፈልጋለን” የሚል ሐሳብ ያለው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሰልጣኞች፣ የቴክኒክ ባለሙያዎችና አትሌቶች የተገኙ ሲሆን ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽ መሰጠቱን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 



Source link

The post የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

Trending Articles