
“የኢትዮጵያንና የሳዑዲ አረቢያ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር ያስፈልጋል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ደመቀ መኮንን
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 08/2013 ዓ.ም (አብመድ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
በኢትዮጵያ የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጀሚል አብዱላህ ጋር ተወያይተዋል፡፡
“የኢትዮጵያንና የሳዑዲ አረቢያ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር ያስፈልጋል” ብለዋል አቶ ደመቀ፡፡
መንግሥት በትግራይ ክልል ያካሄደው የሕግ ማስከበር እርምጃ መጠናቀቁን ተከትሎ የረድኤት ድርጅቶችና የመገናኛ ብዙኃን
በክልሉ እንዲንቀሳቀሱ ምቹ ሁኔታ ስለመፈጠሩ ፣ የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ስለመገንባት፣ ተፈናቃዮችን መልሶ የማቋቋም
ተግባራት እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት ገለልተኛ ተቋማት ከአፍሪካ ሕብረትም ሆነ ከተባበሩት መንግሥታት
ድርጅት ጋር ተባብሮ ለመሥራት መንግሥት ዝግጁ እንደሆነ አብራርተውላቸዋል።
የህዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተም የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አስተባባሪነት
የሦስትዮሽ ድርድሩ እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ፍላጎቷ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በሱዳን እና በግብፅ በኩል እየቀረበ ያለው አዲስ የድርድር ሃሳብ ለኢትዮጵያ ወገን ይፋዊ በሆነ መልኩ ያልቀረበ መሆኑን
አስታውቀዋል፡፡በሀገራቱ መካከል የሚፈጠሩ ልዩነቶች በመርሆዎች መግለጫ ስምምነት መሰረት መፍታት የሚቻል መሆኑን አቶ
ደመቀ አስረድተዋል።
የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ውዝግብ ጋር በተያያዘም፤ ሱዳን የያዘችውን የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ስትለቅ በድርድር ለመፍታት
ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗንም ገልጸዋል።
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በመንግሥት በኩል እየተደረገ ያለውን ጥረት በተመለከተም
ማብራሪያ ሰጥተዋቸዋል።
በኢትዮጵያ የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጀሚል አብዱላህ በበኩላቸው በወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ላይ ለተደረገላቸው ገለጻ
አመስግነዋል፡፡ የሀገራቱን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሠሩም ገልጸዋል።
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ በመንግሥት በኩል እየተደረገ ያለውን ጥረት የሳዑዲ
መንግስት ድጋፍ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
The post “የኢትዮጵያንና የሳዑዲ አረቢያ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር ያስፈልጋል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.