Quantcast
Channel: The Habesha: Latest Ethiopian News, Analysis and Articles
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

Media Expert Kevin Smith Reflects on Experience

$
0
0

U.S. Embassy in Addis Ababa

Scroll down for the Amharic Version of the blog

You don’t have to spend more than a couple of hours talking with an Ethiopian journalist to learn that it’s a daily challenge to ply your trade in a country that calls itself a democracy. The conversations involve a lot of forlorn looks, head shaking and some pent-up anger.
What I’ve come to learn in my handful experiences with African journalists (Sierra Leone, Zambia, Uganda and Ethiopia) is that democracy in theory usually doesn’t translate into a free press in reality. Ethiopia is no exception.
The press is free to work in many of these countries so long as its coverage is complimentary of the government and its usually corrupt politicians.
Threats of imprisonment are common, but, so too are tactics that keep information from the hands of the press and public or officials asserting overwhelming support for state-operated TV, radio and print at the expense of the independent press. All of the tactics to keep the press at bay are in full force in Ethiopia. Couple that with an undertrained workforce of journalists, low pay and an avoidance of standards, and it becomes a bit overwhelming.
Perhaps the greatest among these challenges now is the proliferation of fake news stories either from foreign influencers or the state media. Aided by a population that readily shares unverified information and, the desired effect of manipulating the minds of the masses, is a daily occurrence.

The media landscape is similar to many African countries, but there is a strong online presence from expatriates who want to disseminate questionable news in hopes of staging uprisings against those in power. The government, for its part denounces most news it doesn’t like as fake and metes punishment against legitimate news organizations in some cases.

Whatever the source or the motives, media literacy is needed to help the more than 100 million of the country’s residents sift through the profound static noise that passes for news.

When I traveled there for four days in November my mission was to help scratch the surface of these challenges. I’m thankful neither the U.S. Embassy staff in Addis Ababa, nor the journalists themselves expected a magic bullet solution to the litany of problems. My goal was to help inspire journalists to rise up in voice and to train them and the public on ways to combat the disinformation flooding their daily news feeds.

First, we went after the public and, thanks to a robust U.S. Embassy team and its Facebook presence, we were able to get before 140,000 people on an afternoon to educate them about why fake news is effective, what its intentions are and how to recognize, challenge and defeat its presence on social media.

Later in the week we drilled down on the subject with the journalists and shared with them tools they could use to improve their work, engage the public with transparency about their role and responsibilities and regain credibility.

I also met with representatives of nearly all of the Ethiopian media associations and after three hours of productive discussions, I think some strong alliances were formed. The goal is to join their resources and strengths to work on a nationwide media literacy program that should keep a consistent message in front of the populace for some time.
Despite the obvious up-hill-battle for greater press freedoms many of the Ethiopian journalists I met were decidedly optimistic about their roles, their work and the effect it has with their fellow citizens. Their resolve to tell the truth and be responsible and credible journalists is strong.
I hope with some news ideas, some renewed spirit and inspiration they will move forth a stronger and more viable press. That’s not a magic bullet, but it’s a game plan worthy of execution.

(By Kevin Smith, U.S. Media Expert)

**************//*******////**********

የሚዲያ ባለሙያው ኬቪን ስሚዝና የኢትዮጵያ ቆይታው   የሚዲያ ባለሙያው ኬቪን ስሚዝና የኢትዮጵያ ቆይታው

ዴሞክራሲን በሚያቀነቅን እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሀገር ለጋዜጠኞች የዕለት ሥራን መከወን አዳጋች እንደሆነ ለመረዳት ከአንድ ጋዜጠኛ ጋር ጥቂት ቆይታ ማድረግ በቂ ነው፡፡ ከጋዜጠኛው ፍዝዝ ካለ ዕይታ፤ ራስ መነቅነቅ እና የታመቀ ንዴት የችግሩን አሳሳቢነት በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡

በሴራሊዮን፤ ዛምቢያ፤ ዩጋንዳ እና ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካውያን ጋዜጠኞች ጋር ከነበረኝ ቆይታ የተረዳሁት፤ ዴሞክራሲን በመርህ ደረጃ ማቀንቀን ለነፃ ፕሬስ መስፈን መተማመኛ አለመሆኑን ነው፡፡ በኢትዮጵያም ያለው ሁኔታ ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡

በእነኚህ ሀገራት ያለው ፕሬስ መንግሥትን እና በሙስና የተዘፈቁ ፖለቲከኞቹን እስካወደሰ ድረስ፤ በነፃነት ተንቀሳቅሶ መሥራት ይችላል፡፡

የእስር ማስፈራሪያዎች የተለመዱ እንደመሆናቸው ሁሉ፤ መረጃን ከነፃው ፕሬስ እና ከህዝቡ በመሰወር ወይም ባለስልጣናት በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ላሉ ቴሌቪዥን፤ ራዲዮ እና የህትመት ውጤቶች ብቻ መረጃን በማቀበል ለፕሬስ ነፃነት የቆሙ ያስመስላሉ፡፡ ይህ መረጃን ለነፃው ፕሬስ የመከልከል ስልት፤ በኢትዮጵያም ሙሉ በሙሉ እየተተገበረ ይገኛል፡፡ ጋዜጠኞች ተገቢውን ስልጠና ያለማግኘት፤ አነስተኛ ክፍያ እና ተፈላጊውን መስፈርት ያለማሟላት ጉዳይ ሲጨመርበት ነገሩን ይበልጥ ከባድ ያደርገዋል፡፡

ከተጠቀሱት ተግዳሮቶች ሁሉ የባሰው ደግሞ ከውጭ በሚኖር ጫና ወይም በመንግሥት ቁጥጥር ስር ካሉ ሚዲያዎች የሚሰራጨው የሀሰት ወሬ ነው፡፡ ያልተረጋገጠ ወሬን ለመለዋወጥ በጉጉት የሚጠብቅ ተጠቃሚ ህብረተሰብ የሚፈጥረው የተመቻቸ ሁኔታ እና የተጠቃሚውን አስተሳሰብ እንደፈለጉ የመቃኘቱ ጉዳይ የየዕለት ሁነት ነው፡፡
የሚዲያ ምህዳሩ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ካለው ተመሳሳይነት ቢኖረውም፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በመንግሥት ላይ አመጽ ማነሳሳትን በማለም ተአማኒነት የሌላቸውን መረጃዎች ጭምር በመጠቀም ጠንካራ የመረጃ መረብ ዘመቻ ያካሂዳሉ፡፡ መንግሥት በበኩሉ የማይፈልጋቸውን ዜናዎች ሀሰተኛ በማለት ይፈርጃቸዋል፡፡ በአንዳንድ አጋጣሚዎችም በህጋዊ የዜና አውታሮች ላይ የቅጣት እርምጃ ይወስዳል፡፡
መነሻው ወይም ዓላማው ምንም ይሁን ምን፤ ከ100 ሚሊዮን የሚልቁት የሀገሪቱ ዜጎች፤ አማራጭ የመረጃ ምንጭ ይኖራቸው ዘንድ በተሻለ የሚዲያ ዕውቀት ሊታገዙ ያስፈልጋቸዋል፡፡
በህዳር ወር በነበረኝ የአራት ቀናት ቆይታ፤ እነኚህን ችግሮች በጥቂቱ ለመነካካት ችለን ነበር፡፡ ለተጠቀሱት ችግሮች የአዲስ አበባው የአሜሪካ ኤምባሲ ሰራተኞችም ሆኑ ያገኘዋቸው ጋዜጠኞች፤ የመጨረሻ ነው የተባለ መፍትሔ ባለመጠበቃቸው አመሰግናቸዋለሁ፡፡ ዓላማዬ የነበረው ጋዜጠኞች ድምጻቸው እንዲሰማ ማገዝ እና እነርሱንም ሆነ ህዝቡን ያለማቋረጥ የሚደርሳቸውን የተሳሳተ መረጃ መቋቋም የሚችሉበትን መንገድ ላይ ግንዛቤ መፍጠር ነው፡፡
በመጀመሪያ ቆይታ የነበረን ከህዝቡ ጋር ነበር፡፡ ለአሜሪካ ኤምባሲ አባላት እና ሰፊ ተደራሽነት ላለው የፌስቡክ ገጻቸው ምስጋና ይሁንና፤ በከሰዓቱ ክፍለ ጊዜ በነበረን ትምህርት ወደ 140,000 ለሚሆኑ ሰዎች በማኅበራዊ ሚዲያ አማካይነት ስለሀሰተኛ ወሬ ቅቡልነት፤ ዓላማው እና እንዴት ሀሰተኛ ካልሆነው መለየት እንደሚቻ እንዲሁም ከማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል ግንዛቤ ሰጥተናል፡፡
በመቀጠል ከጋዜጠኞች ጋር ሥራቸውን ስለሚያሻሽሉበት መንገድ እንዲሁም ስለሚናቸው እና ሃላፊነታቸው ህዝቡን በግልጽ በማወያየት በህዝቡ ዘንድ የነበራቸውን ተዓማኒነት መልሰው እንዲያገኙ የሚያስችል የሃሳብ ልውውጥ አድርገናል፡፡
ከኢትዮጵያ የሚድያ ማህበራት ተወካዮችም ጋር የተገናኘሁ ሲሆን፤ በነበረን የሶስት ሰዓት ቆይታ መልካም የሚባል ትብብር ፈጥረናል፡፡ ዓላማውም፤ ያለውን ሀብት እና ጠንካራ ጎን በጋራ ጥቅም ላይ በማዋል፤ ለህዝቡ ወጥነት ያላቸውን መልዕክቶች በማቅረብ የሚዲያ እውቀት እንዲዳብር ማስቻል ነበር፡፡
የተሻለ የፕሬስ ነጻነትን ማስፈን ፈተና በሆነበት በዚህ ወቅትም፤ ያገኘኋቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ስለ ሚናቸው፤ ሥራቸው እና ስለሚያመጣው ለውጥ ብሩህ ተስፋን ሰንቀዋል፡፡ እውነትን ለመጋፈጥ፤ ሃላፊነት ለመውሰድ እና በህዝቡ ዘንድ ተአማኒነትን ለማትረፍ ቁርጠኛ ናቸው፡፡
በአዲስ አስተሳሰብ፤ አዲስ መንፈስ እና ተነሳሽነት ጠንካራ ፕሬስ እንደሚፈጥሩ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡ ይህ ጠቀሜታው የላቀ የጨዋታ ህግ እንጂ አንድ ወጥ መፍትሔ አይደለም፡፡
(ኬቪን ስሚዝ አሜሪካዊ የሚዲያ ባለሙያ ነው)
(በጦማሩ የተካተተው ሀሳብ እና አመለካከት የአሜሪካንን መንግሥት አቋም አያንጸባርቅም)

Source: U.S. HOW EMBASSY ADDIS ABABA

The post Media Expert Kevin Smith Reflects on Experience appeared first on Satenaw: Ethiopian News|Breaking News: Your right to know!.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

Trending Articles