Quantcast
Channel: The Habesha: Latest Ethiopian News, Analysis and Articles
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

ይድረስ ለፋሽስቱ ህወሃትና ግብረ በላዎቹ “አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” –“አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል” እንዳይሆን !

$
0
0

 

31በቅድሚያ ልሳነ ግፉዓን እንደ ድርጅት በይፋ ከተመሰረተበት ከ 2009 (እኤአ) ጀምሮና ይልቁንም በሙሉ ሃይላችን ወደ ትግል ከገባንበት ከ2013 (እኤአ) ጀምሮ በተከታታይ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ለዓለም ማህበረሰብ ስናቀርብ የነበርነውን አቤቱታ፣ የድረሱልን ጩሃትና፣ የአግዙን ጥሪ ተቀብላችሁ ያለምንም ማቅማማት ከወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ማህበረሰብ ፍትሃዊ የህልውና ትግል ጎን ለተሰለፋችሁ የትግል አጋሮቻችንና ወዳጆቻችን ሁሉ ከመራራው ትግላችን ጎን በቁርጠኝነት በመሰለፍ ጥያቄያችንን አንግባችሁ ለከፈላችሁትና እየከፈላችሁት ላለው ውድና ክቡር መስዋዕትነት በህዝባችን ስም ላቅ ያለው ምስጋናችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ።

እንዲሁም ዘራችንን ለማጥፋትና በትግሪያዊነት ለመተካት አቅዶና ተዘጋጅቶ እርስታችንን በመውረር የዘር ማፅዳት ወንጀል የፈፀመብን ጠላታችን የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ቡድንና በዚህ ፋሽስትና ተስፋፊ ድርጅት ዙሪ የተሰባሰባችሁ ግብረ በላዎች ሁሉ በህዝባችን ላይ የቃጣችሁትን ፈርጀ ብዙ ጥቃት ታቆሙና ከእኩይ ተግባራችሁ በአስቸኳይ ትታቀቡ ዘንድ የመጨረሻ ወደ ጤናማ ህሊና መመለሻ ደወልና በታሪክም ይመዘገብ ዘንድ ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን ይህን ጥብቅ ግልፅ መልዕክት ማስተላለፍ ይሻል።

ጀግናው ህዝባችን “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ” ቡድን ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ ዕርስታችንን በወረራ ከያዘ ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት ድረስ በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለው የዘር ማጽዳትና አካባቢያችንን በትግሬያዊነት የመተካት ፈርጀ ብዙ ወንጀል በመቃወምና፣ ከአባቶቹ የወረሰውን ለወራሪና ለባንዳ የእግር እሳት የመሆን ማንነቱን ሊተገብር ከሁሉም አስቀድሞ “ከፋኝ” በማለት ጀግኖቹን ከፊት አስቀድሞ ሲፋለም መኖሩ ይታወቃል።

ዛሬም ህዝባችን ከምንግዜውም በላይ እራሱን አደራጅቶና አጠናክሮ ዘሩን ከጥፋትና የአባቶቹን እርስት ከባንዳዎች ወረራ ለመታደግ እያደረገ የሚገኘው ፍትሃዊ ትግል የፋሽስቱን ህወሃትና የጀሌዎቹን ጎራ እያንኮታኮተውና እያሽመደመደው የሚገኝ ሲሆን፣ በአንፃሩ ደግሞ በህዝባችን ቁጣ ጉሮሮው የታነቀው የባንዳው መንደር የሚይዘውንና የሚጨብጠውን በማጣት አንዴ በ“ጥልቅ መታደስ” ሌላ ጊዜ በ“አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” ስም ጭቆናውንና ወረራውን ለማስቀጠል “አራምባና ቆቦ” እየዳከረ ይገኛል።

በሃገራችን ኢትዮጵያና በተለይም ዘሩን ከፈፅሞ ጥፋት ለመታደግ የሞት ሽረት ትግል ላይ በሚገኘው ህዝባችን ላይ ከመስከረም 28, 2009 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን በወራሪው የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን ፊት አውራሪነት የታወጃው የ“አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” የህዝብን ጥያቄ በፍትሃዊ መንገድ ለመመለስና ሃገርንና ህዝብን ለማረጋጋት የታለመ እንዳልሆነ ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን በፅኑ ያምናል።

ይልቁንም ይህ የቁጩ አዋጅ ከዚህ ቀደም የህዝብን ሰላማዊ ጥያቄና ቁጣ በአዋጅና በህጋዊነት ስም ለማፈንና ለመብታቸው የሚታገሉ ንጹሃን ዜጎችንና የህዝብን ሰላማዊ መሪዎች ለማሰር፣ ለማሰደድና፣ ብሎም ለመግደል ተግባር ላይ እንደዋሉት “የሙስና”፣ የ“የፀረ-ሽብር”ና መሰል አፋኝና እርባና ቢስ አዋጆች ሁሉ፣ ዛሬም በመላው ሃገራችን የተቀጣጠለውን የፍትህና የህልውና ጥያቄ በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ህዝብን ለከፋ ቁጣና ወደ ተቀናጀ ህዝባዊ አመፅ የሚያስግቡ ከዘመኑና ከህዝባችን ንቃተ ህሊና ጋር የማይመጣጠኑና እጅግ ኋላቀር እንደሆኑት የቀደሙት “አዋጆች” ቀጣይ የጥፋት መንገድ እንደሆነ እንረዳለን።

ቀደም ባሉት ጊዜያት ህዝባችን ላነሳቸው ፍትሃዊ ጥያቄዎች ያለምንም ማቅማማትና መፈራገጥ ያልተሸራረፍ ምላሽ መስጠት ብቸኛ መፍትሄ መሆኑን አበክረን ማሳሰባችን ይታወቃል። ይልቁንም ዛሬም ትንሽም ብትሆን የቀረችውን ክልላዊም ሆነ ሃገራዊም ሰላምና መረጋጋት ማቆየትና ከሚንቀለቀለው ህዝባዊ ቁጣ መዳን የሚቻለው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ህዝባችን በተደጋጋሚ የነሳቸውን ፍትሃዊና ህጋዊ ጥያቄዎች በአስቸኳይ ምላሽ መስጠትና ተግባር ላይ ማዋል ሲቻል ብቻ ነው ብሎ ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን አጥብቆ ያምናል።

ዛሬ የህወሃትን መቀመጫ ያሞቀውና መሪዎቹንም ሆነ ፍርፋሪ ለቃሚዎቹን እንደ አበደ ውሻ የሚያክለፈልፋቸውና “ኮሽ” ባለ ቁጥር ከቦታ ቦታ “ቅልና ቋንቁራ” ሳይቀር እየሰበሰቡ የሚያንከራትታቸው ገና በህዝባዊው ቁጣ የ“ሙከራ ጊዜ” ወቅት መሆኑ በእጅጉ ግርምትን የሚፈጥር ከምሆኑም በላይ ለዘመናት ታላቁን ህዝባችን በማሸበር ሲያስጨንቁትና ሲበዘብዙበት የኖሩባቸው “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ”፣ “እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ ተበታተናለች”ና ሌሎችም የማስፈራሪያ ተረቶቻቸው ህዝባችን በቁጣ ሲነሳ እንደጉም በነው ሲጠፉ መታዘብ ችለናል።

ይሃውም ይህን መግለጫ እስካወጣንበት እለት ያለው የህዝባችን ትግልና ተቃውሞ ለዋናውና እየመጣ ላለው፣ እንደ እሳተ ጎሞራ ለሚፋጀው የህዝብ ቁጣ መንገድ ጠራጊ እንጂ ዋናው የህዝባችን የቁጣ ሰይፍ  እንዳልሆነ በአፅንኦት መግለጥ እንሻለን። ይህ እውነተኛውና የከፋው የህዝብ ብሶትና ቅጣት ሲገለጥ ከፊት የሚቆምም ሆነ ከቁጣው መቅስፍት የሚተርፍ አንዳችም የህወሃት ሰራዊትም ሆነ ግብረ-በላ ጀሌ እንደማይኖር በእርግጠኝነት መናገርን ወደድን። ምንግዜም ቢሆን ብሶት የወለደው የህዝብ ትግል ያለጥርጥር አሸናፊ ነውና!

 

ስለዚህ ይህን አላስፈላጊ የህዝብ ቁጣ ለማስተናገድ ከመሞከርና የቀሩትን እጅግ ጠባብና አነስተኛ የመዳኛ መንገዶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዳይከፈቱ ሆነው ከመዘጋታቸው በፊት የሚከተሉትን የመፍትሄ እርምጃዎች በትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ቡድንና በግበረ-በላዎቹ በኩል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲተገበሩ ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን አጥብቆ ያሳስባል።

1ኛ. ከወልቃይት ጠገዴና ጠለምት፣ ከጎንደር፣ ከጎጃምና፣ ከአዲስ አበባ ታፍነው የተወሰዱና በትግራይ፣ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በቤንሻንጉልና፣ በአዲስ አበባ የማጎሪያና የማሰቃያ ቦታዎች ተግዘው የሚገኙ ወገኖቻችን በአስቸኳይ መልቀቅና ይህንም እርምጃ በሃገሪቱ ሚዲያ ወጥቶ ለህዝብ በግልፅ ማሳወቅ፣

2ኛ. ከመላው ኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ ታፍነው ለእስርና ለስቃይ የተዳረጉ የፖለቲካ እስረኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የመብት ተሟጋቾችና፣ የሃገር ሽማግሌዎችና የማህበረሰብ ተጠሪዎች እንዲሁ በአስቸኳይ እንዲፈቱና ይህንም እርምጃ በሃገሪቱ ሚዲያ በኩል ለህዝብ በግልፅ ማሳወቅ፣

3ኛ. በመስከረም 28, 2009 ዓ.ም ጀምሮ ተግባር ላይ እንዲውል የታወጀው የ“አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” በአስቸኳይ እንዲነሳ፣ በሃገር አቀፍ ደረጃ ተቋቁሟል የተባለው “ኮማንድ ፖስት” በይፋ እንዲበተንና ለዚህም ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ አዋጁን ለህዝብ የገለጠው አካል በሃገሪቱና አዋጁ በተላለፈባቸው የውጭ ሚዲያዎች ቀርቦ አዋጁ መሻሩን ለህዝብ በግልፅ እንዲያሳውቅ፣

4ኛ. በጎንደር፣ በጎጃምና፣ በኦሮሚያ ውስጥ የተቋቋመው “ኮማንድ ፖስት” በይፋ እንዲዘጋና በሰላማዊ ህዝብ መካከል ሰፍሮ የሚገኘው ጦር ሰራዊት በአስቸኳይ ወደ ካምፑ እንዲመለስና አካባቢዎቹን የማስተዳደርና የመጠበቅ ስራ ለመደበኛ ሲቪል አስተዳደር እንዲመለስና ለከተማ ፖሊስ አባላት ብቻ እንዲተው፣

5ኛ. አሁን ስራ ላይ ያለው የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት እንዲበተንና ስልጣን ላይ ያለው ቡድን ከህዝብ በሃይል የወሰደውን ስልጣን ከህዝብ ለተወጣጣና ነፃነቱ በገለልተኛ አካላት ለተረጋገጠ ጊዜያዊ ባለ አዳራ መንግስት ስልጣኑን እንዲያስረክብ፣

6ኛ. እነዚህ ከ1ኛ – 5ኛ ተራ ቁጥር የተዘረዘሩ እርምጃዎች እስከ ጥቅምት 16, 2009 ዓ.ም ለህዝብ ይፋ ሆነው ተግባር ላይ የማይውሉ ከሆነ ማንኛውም የህዝብ ወገን የሆነ የብአዴን አባል በይፋ ከህወሃት መራሹ መንግስት በመለየትና ህዝባዊ ትግሉን በመቀላቀል እራሱን እንዲያድንና ወገኑን ከጥቃት ይከላከል ዘንድ አጥብቀን እናሳስባለን።

በመጨረሻም

ከላይ በግልፅ የተቀመጡት እርምጃዎች በወቅቱ ማለትም እስከ ጥቅምት 16, 2009 ዓ.ም ባለመወሰዳቸው ምክንያት ለሚደርሱት ሃገራዊም ሆነ ክልላዊ ጥፋቶች ስልጣን ላይ ያለው ህወሃት መራሹ ቡድን ዛሬም እንደ ቀደሙት ጊዜያት ሁሉ ሙሉ ሃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን በአፅንኦት ማስጠንቀቅ እንሻለን።

 

ድል የህዝብ ነው!

ልሳነ ግፉዓን ድርጅት

ጥቅምት 9, 2009 ዓ.ም

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13041

Trending Articles